1 ሳሙኤል 12:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “አላታለልኸንም ወይም ግፍ አልሠራህብንም፤ ከማንም እጅ አንዳች ነገር አልተቀበልህም” ብለው መለሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “አላታለልኸንም ወይም ግፍ አልሠራህብንም፤ ከማንም እጅ አንዳች ነገር አልተቀበልህም” ብለው መለሱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም “ከቶ አላታለልከንም፤ አልጨቈንከንም፤ ከማንም ሰው ምንም ነገር አልወሰድክም” ሲሉ መለሱለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሳሙኤልን፥ “ግፍም አላደረግህብንም፤ የቀማኸን የለም፤ አላሠቃየኸንም፤ ከእኛም ከማንም እጅ ምንም አልወሰድህም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ አልሸነገልኸንም፥ ግፍም አላደረግህብንም፥ ከሰውም እጅ ምንም አልወሰድህም አሉ። |
ድሜጥሮስ በሁሉም ተመስክሮለታል፤ እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች፤ እኛም እንመሰክርለታለን፤ ምስክርነታችን ደግሞ እውነት እንደሆነ ታውቃለህ።
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”
ሳሙኤልም፥ “በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ ጌታና እርሱ የቀባው ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው” አላቸው። እነርሱም፥ “እርሱ ምስክር ነው” አሉ።