1 ሳሙኤል 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡ ሳሙኤልን፥ “ሳኦል እንዴት ሊገዛን ይችላል! ያሉት እነማን ነበሩ? እነዚህን ሰዎች እንገድላቸው ዘንድ አምጣቸው” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ሳሙኤልን፣ “ ‘ሳኦል እንዴት ሊገዛን ይችላል!’ ያሉት እነማን ነበሩ? እነዚህን ሰዎች እንገድላቸው ዘንድ አምጣቸው” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሳሙኤልን “ሳኦል በእኛ ላይ አይነግሥብንም ያሉት ሰዎች እነማን ናቸው? እነርሱን አሳልፈህ ስጠንና እንግደላቸው!” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ሳሙኤልን፥ “ሳኦል አይንገሥብን ያሉ እነማን ናቸው? እነዚያን ሰዎች አውጡአቸውና እንግደላቸው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ሳሙኤልን፦ ሳኦል አይንገሥብን ያሉ እነማናቸው? አውጡአቸውና እንግደላቸው አሉት። |
አንዳንድ ሥርዓተ አልባዎች ግን፥ “እንዲህ ያለ ሰው እንዴት ሊያድነን ይችላል?” በማለት ናቁት፤ ስጦታም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።