1 ሳሙኤል 11:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያቢሽም ሰዎች፥ “እኛ ነገ እጃችንን እንሰጣችኋለን፤ እናንተም መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ ልታደርጉብን ትችላላችሁ” አሏቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኢያቢስም ሰዎች፣ “እኛ ነገ እጃችንን እንሰጣችኋለን፤ እናንተም መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ ልታደርጉብን ትችላላችሁ” አሏቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያቤሽም ሰዎች አሞናውያንን “ነገ እጃችንን ለእናንተ እንሰጣለን እናንተም በእኛ ላይ የምትፈልጉትን አድርጉ” አሉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢያቢስም ሰዎች፦ ለአሞናዊው ናዖስ “ነገ እንወጣላችኋለን፤ ደስ የሚያሰኛችሁንም አድርጉብን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአያቢስም ሰዎች፦ ነገ እንወጣላችኋለን፥ ደስ የሚያሰኛችሁንም አድርጉብን አሉ። |
ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፥ “ለያቢሽ ገለዓድ ሰዎች፥ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለያቢሽ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ እጅግ ተደሰቱ።