1 ሳሙኤል 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፊቴ ቀድመህ ወደ ጌልገላ ውረድ፤ እኔም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነትት መሥዋዕቱን ለማቅረብ ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ወደ አንተ መጥቼ ምን ማድረግ እንዳለብህ እስክነግርህ ድረስ ግን ሰባት ቀን መቆየት አለብህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከፊቴ ቀድመህ ወደ ጌልገላ ውረድ፤ እኔም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቱን ለማቅረብ ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ነገር ግን ወደ አንተ መጥቼ ምን ማድረግ እንዳለብህ እስክነግርህ ድረስ ሰባት ቀን መቈየት አለብህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቃጠለውንና የደኅንነት መሥዋዕት ለማቅረብ አንተን ወደማገኝበት ወደ ጌልጌላ ቀድመኸኝ ትሄዳለህ፤ እኔ መጥቼ ምን ማድረግ እንደሚገባህ እስክነግርህ ድረስ ለሰባት ቀን በዚያው ቈይ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደርገውን እስከምነግርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈያለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፥ እኔም፥ እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፥ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደረገውን እስክነግረህ ድረስ ሰባት ቀን ትቆያለህ። |
ከሰላሙም መሥዋዕት ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ የሚያቀርበው፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ላቱን ሁሉ፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥
እስራኤላውያን ሁሉ፥ “ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር ሰፈር መታ፤ እስራኤልም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ የተጠሉ ሆኑ” የሚለውን ወሬ ሰሙ። ሕዝቡም ከሳኦል ጋር ለመሰለፍ ወደ ጌልገላ ተሰበሰቡ።
ሳሙኤልም፥ “ሰይፍህ ሴቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፥ እናትህም በሴቶች መካከል ልጅ አልባ ትሆናለች” ሲል አጋግን ጌልገላ ላይ በጌታ ፊት ቆራረጠው።