ሮማውን ነገሩን ባወቁ ጊዜ አንድ የጦር መሪ ብቻ ልከው ጦርነት ገጠሟቸው፤ ከግሪካውያን ብዙዎች ሞቱ፤ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው በውርስ ተወሰዱ፤ ሮማውያን ንብረታቸውን ዘርፈው ወሰዱባቸው፤ አገራቸውን አስገበሩ፤ ምሽጐቻቸውን አፈረሱ፤ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲያገለግሏቸው አድርገዋቸዋል።