እንስሶቹ በእግረኛ ጦር መካከል ተከፋፈሉ፤ በእያንዳንዱ ዝሆን አጠገብ የብረት ልብስ የለበሱና የራስ ቁር ያደረጉ ወታደሮች ተሰልፈው ቆሙ፤ እንዲሁም አምስት መቶ ምርጥ ፈረሰኞች በእያንዳንዱ ዝሆን ጐን ተሰለፉ።