ሕዝቡ የስምዖን ታማኝነትና ለራሱ ሕዝብ ሊሰጥ ያሰበውን ክብር ተመለከተለት፤ ባደረገው ሁሉ፥ ለሕዝቡ ባሳየው እውነተኛነትና እምነት ምክንያት የእነርሱ መሪና ሊቀ ካህናት እንዲሆን አደረገጉት፤ ምክንያቱም የእርሱ የዘወትር ጥረቱ ሕዝቡን ከፍ ለማድረግ ነበረ።