እነርሱ የገለጹልንን በሕዝቡ ውሳኔዎች መካከል እንዲህ ስንል ጽፈነዋል፤ የአንጥዮኩስ ልጅ ኑመንዮስና የኢያሶን ልጅ አንጢጰጥሮስ የአይሁድ መልእክተኞች ሆነው ከእኛ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት ለማደስ ወደ እኛ መጥተዋል፤