ከዚህ በኋላ ትሪፎን ሀገሪቱን ለመውረርና ለማጥፋት ገሠገሠ፤ ወደ አዶራ በሚወስደው መንገድ ዞሮ ሄደ፤ ግን ስምዖንና የእርሱ ሠራዊት እርሱ በሄደበት ሁሉ እየተከታተሉ ይቃወሙት ነበር።