ወደ አዛጦን ለመድረስ በተቃረበ ጊዜ የዳጐን ቤት መቃጠሉን፥ አዛጦንና አካባቢዎችዋ መደምሰሳቸውን፥ ሬሳዎች በዚህም በዚያም መጣላቸውን፥ ንጉሡ በሚያልፍበት ቦታ ሰብስበውና ደራርበው አስቀምጠዋቸው ስለ ነበር በውጊያው ጊዜ ተቃጥለው የነበሩትን ሰዎች ቅሪቶቻቸውንም አሳዩት።