1 ነገሥት 6:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ከውስጥ ሰፋ፥ ከውጪ ጠበብ ያሉ መስኮቶች ነበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለቤተ መቅደሱም ባለዐይነ ርግብ መስኮቶች አበጀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ከውስጥ ሰፋ፥ ከውጪ ጠበብ ያሉ መስኮቶች ነበሩት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቤቱም በዐይነ ርግብ የተዘጉ መስኮቶችን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቤቱም በዐይነ ርግብ የተዘጉ መስኮቶች አደረገ። |
ጓዳዎቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ ትናንሽ መስኮቶች ነበሩአቸው፤ ደግሞም በመተላለፊያው ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።
የቤቱ መግቢያዎች፥ ጠባቦቹ መስኮቶች፥ በዙሪያቸው የነበሩ ሦስት መተላለፊያዎች፥ የቤቱ መግቢያ ዙሪያውን ከመሬት ጀምሮ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት ተለብጦ ነበር፤ መስኮቶቹም የተሸፈኑ ነበሩ፤