1 ነገሥት 14:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥር እንጀራ፥ ጥቂት ሙልሙል ዳቦና አንድ ገንቦ ማር ውሰጂለት፤ ስለ ልጁ ሁኔታ እርሱ ይነግርሻል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትሄጂም ዐሥር እንጀራ፣ ጥቂት ሙልሙል ዳቦ እና አንድ እንስራ ማር ይዘሽ ሂጂ፤ እርሱም በልጁ ላይ የሚደርሰውን ይነግርሻል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሥር እንጀራ፥ ጥቂት ሙልሙል ዳቦና አንድ ገንቦ ማር. ውሰጂለት፤ ስለ ልጁ ሁኔታ እርሱ ይነግርሻል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእጅሽም ለእግዚአብሔር ሰው ዐሥር እንጀራና የወይን እሸት አንድም ማሠሮ ማር ይዘሽ ወደ እርሱ ሂጂ፤ በልጁም የሚሆነውን ይነግርሻል” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእጅሽም ዐሥር እንጀራና እንጎቻዎች አንድም ምንቸት ማር ይዘሽ ወደ እርሱ ሂጂ፤ በልጁም የሚሆነውን ይነግርሻል፤” አላት። |
በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቆሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ።
ሌላም ጊዜ በዓልሻሊሻ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው በመከር ጊዜ በመጀመሪያ ከተወቃው ገብስ የተጋገሩ ኻያ የዳቦ ሙልሙሎችና አዲስ የተቆረጠ እሸት ለኤልሳዕ ይዞለት መጣ፤ ኤልሳዕም “ለነቢያት ጉባኤ አቅርብላቸውና ይብሉ” ብሎ አገልጋዩን አዘዘው፤
ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።
ንጉሡም “ይህን ደብዳቤ ይዘህ ወደ እስራኤል ንጉሥ ሂድ” ብሎ ፈቀደለት። ስለዚህም ንዕማን ሠላሳ ሺህ ጥሬ ብር፥ ስድስት ሺህ መሐለቅ ወርቅና ምርጥ የሆነ ዐሥር መለወጫ ልብስ አስጭኖ፥ ጉዞውን ቀጠለ፤
በማዕድም ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በራሱ ላይም አፈሰሰችው።