1 ነገሥት 1:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፥ ኢዮአብም የቀንደ መለከት ጽምፅ በሰማ ጊዜ፦ “ይህ በከተማ ውስጥ ያለ የሽብር ድምፅ ምንድነው?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዶንያስና የተጠሩት እንግዶች ሁሉ ግብዣውን በማገባደድ ላይ ሳሉ፣ ይህንኑ ሰሙ፤ ኢዮአብም የመለከቱን ድምፅ ሲሰማ፣ “ይህ በከተማዪቱ ውስጥ የሚሰማው ድምፅ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዶንያስና የጠራቸው ተጋባዦች ሁሉ ግብዣውን በማገባደድ ላይ ሳሉ የሁካታ ድምፅ ሰሙ፤ ኢዮአብም የእምቢልታ ድምፅ በሰማ ጊዜ “ይህ በከተማው ውስጥ የሚሰማው የሁካታ ድምፅ ሁሉ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፤ ኢዮአብም የመለከት ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “ይህ በከተማ የምሰማው ድምፅ ምንድን ነው?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፤ ኢዮአብም የቀንደ መለከት ጽምጽ በሰማ ጊዜ “ይህ በከተማ ውስጥ ያለ የሽብር ድምጽ ምንድር ነው?” አለ። |