1 ዜና መዋዕል 6:70 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዓኔርንና መሰማሪያዋን፥ ቢልዓምንና መሰማሪያዋን፥ ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ተሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ሰጧቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምዕራብ በኩል ባለው በምናሴ ግዛት ደግሞ የዓኔርና የቢልዓም ከተሞች በዙሪያቸው ካሉት የግጦሽ ቦታዎች ጋር ለቀሩት ለቀዓት ጐሣ ቤተሰቦች ተመድበውላቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዓኔርንና መሰማሪያዋን፥ ቤልዓምንና መሰማሪያዋን፥ ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምናሴም ነገድ እኵሌታ ዓኔርንና መሰማርያዋን፥ ቢልዓምንና መሰማርያዋን፥ ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ። |
በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ዓይነዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ታዕናክና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ መጊዶና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ሦስቱ ኮረብቶች ለምናሴ ነበሩ።