1 ዜና መዋዕል 26:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሒኤሊ ልጆች፤ በጌታ ቤት በቤተ መዛግብት ላይ ተሹመው የነበሩት ዜቶም፥ ወንድሙም ኢዮኤል ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሒኤሊ ወንዶች ልጆች፣ ዜቶምና ወንድሙ ኢዩኤል። እነዚህም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ኀላፊዎች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዜታምና ኢዮኤል የተባሉት የይሒኤል ሌሎች ሁለት ልጆች የቤተ መቅደሱ ቤተ መዛግብትና የዕቃ ግምጃ ቤቶች ኀላፊዎች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሔኤሊ ልጆች፤ በእግዚአብሔርም ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብት ላይ የነበሩ ዜቶም፥ ወንድሙም ኢዮኤል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሒኤሊ ልጆች፤ በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብት ላይ የነበሩ ዜቶም፥ ወንድሙም ኢዮኤል። |
ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፥ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።