2 ጴጥሮስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ኀጢአት ለሚያደርጉ ሁሉ ምሳሌ እንዲሆኑ፣ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ ከፈረደባቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአትንም እያደረጉ ላሉት ምሳሌ እንዲሆን፤ የሰዶምንና ገሞራን ከተማዎች አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ከፈረደባቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም እግዚአብሔርን ለማያመልኩ ሁሉ የመቀጣጫ ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ እንዲጠፉ ፈረደባቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥ |