2 ጴጥሮስ 2:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው፦ አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሮች ሆነው ሳሉ፣ ሌሎችን ነጻ ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለተገዛለት ለዚያ ነገር ባሪያ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሳቸው የጥፋት ባርያዎች ሆነው “ነጻ ትወጣላችሁ፤” እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ የተገዛ ባርያ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነጻ ትወጣላችሁ” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል። ሰው ሲሸነፍ ላሸናፊው ባሪያ ሆኖ ስለሚገዛ እነርሱም ራሳቸው የኃጢአት ባሪያዎች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው “አርነት ትወጣላችሁ፤” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና። |