2 ጴጥሮስ 2:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፥ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንቱ ቃል እየደረደሩ በስሕተት ከሚኖሩት መካከል አምልጠው የመጡትን ሰዎች በሴሰኛ ሥጋዊ ምኞት በማባበል ያታልላሉና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንቱና የትዕቢት ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት ለጥቂት ያመለጡትን ሰዎች በሥጋ ሴሰኛ ምኞት በማታለል ያስታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስሕተት ከሚኖሩት ሰዎች መካከል አምልጠው ከመጡ ገና ብዙ ያልቈዩትን ሰዎች ከንቱ የሆነ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወትና በሴሰኛነት በማባበል ያታልሉአቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ። |