ነገር ግን ገናና የሆነው እግዚአብሔር ከፈቀደ፥ የጥበብንም መንፈስ ካሳደረበት፥ እርሱ የጥበቡን ነገር ያፈልቃል፤ በጸሎቱም ለእግዚአብሔር ይገዛል።
የታላቁ እግዚአብሔር ፈቃድ ይህ ከሆነ፤ እርሱ በእውቀት መንፈስ ይሞላል፥ የጥበብን ቃላት ያዘንበል፥ በጸሎቱም እግዚአብሔርን ያመሰግናል።