ያቀረቡልህን እንደ ብልህ ሰው ሁነህ ብላ፤ ባልንጀራህን እንዳታስጸይፍ ስታላምጥ ምላስህን አታጩህ።
እርሱን የሚወድትን ሁሉ የአምላክ ዐይኖች ይከታተላሉ። የማይደፈረው ጠባቂያቸው፥ ጠንካራውም ደጋፊያቸው እርሱ ነው። የበረሃው ነፋስ ከለላ፥ የቀን ሐሩር ጥላ፥ ከመከራ ጠባቂ፥ ከውድቀታቸውም አዳኛቸው ነው።