እኩሌታውን ቢከፍልህ በጭንቅ ነው፤ ዳግመኛም ያንኑ በምድር ላይ ወድቆ ያገኘኸው ይመስልሃል፤ ይህስ ካልሆነ ገንዘብህን ሁሉ ታጣለህ፤ ዳግመኛም ጠላት ይሆንሃል፤ ርግማንንና ስድብን ይከፍልሃል፤ ከሚያከብርህም ይልቅ ያዋርድሃል።
እንዲከፍል ቢገደድ እንኳ አበዳሪው ግማሹን ብቻ ቢያገኝ ነው፤ ያንንም እንደ ትልቅ ዕድል ይቆጥረዋል። ካልሆነ ግን ገንዘቡን ተነጥቆ በራሱም ላይ ጠላትን ያፈራል። ወሮታውም፥ እርግማንና ውርደት በክብርም ፈንታ ስድብ ይሆናል።