የከበደ ሸክምን አንሥተህ በራስህ አትሸከም፥ ገንዘብህንም ከሚበረታብህና ከባለጸጋ ገንዘብ ጋራ አትጨምር፥ የሸክላ ድስት ከብረት ድስት ጋር በየት አንድ ይሆናል? እርስዋ መትታ እርስዋ ትጮኻለችና፥ እርስዋም ትሰብራለችና።
ከአቅምህ በላይ የሆነን ሸክም ለማንሳት አትሞክር፤ ከአንተ የበለጠ ኃያልና ሃብታም ከሆነው ጋር አትጎዳኝ፤ ስለምን የሸክላውን ማሰሮ ከብረት ድስት ጎን ታኖራልህ? ሁለቱ ሲጋጩ ይሰበራልና።