በተቸገርህም ጊዜ እያመሰገነ ያገለግልሃል፤ ሰውነትህን አጽናት፤ ከእርሱም ተጠበቅ፤ እንደዛገ መስታወት ትሆንበታለህ፤ ፈጽሞም አይችልህም።
ትሑት ቢመስልና አንገቱን ቢደፋም፥ ቁጥብነትህን ግፋበት፤ ጥንቃቄም አድርግበት፥ በሱ ዘንድ መስተዋት እንደሚወለውል ሁን፤ ዝገቱም እስከ መጨረሻም እንደማይዘልቅ እወቅ።