የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ራእይ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቍ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ተቀምጦም የነበረው የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንይመስል ነበር። የመረግድ ዕንየመሰለ ቀስተ ደመናም ዙፋኑን ከብቦት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቁ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የነበረው መልኩ የኢያሰጲድንና የሰርዲኖን ዕንቊ ይመስል ነበር፤ በዙፋኑም ዙሪያ የመረግድ ዕንቊ የመሰለ ቀስተ ደመና ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ተቀምጦም የነበረው በመልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቍ ይመስል ነበር። በመልኩም መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና በዙፋኑ ዙሪያ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት



ራእይ 4:3
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቆ​መ​በ​ትን ቦታ አዩ፤ ከእ​ግ​ሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚ​ያ​በራ፥ እንደ ብሩህ ሰን​ፔር ድን​ጋይ የሚ​መ​ስል ወለል ነበረ።


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ተራ በሉር፥ ሰን​ፔር፥ ኢያ​ሰ​ጲድ፤


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ተራ በሉር፥ ሰን​ፔር፥ ኢያ​ሰ​ጲድ፤


ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ ዖዝ​ያን በሞ​ተ​በት ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በረ​ዥ​ምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀ​ምጦ አየ​ሁት፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ቤቱን ሞል​ቶት ነበር።


በራ​ሳ​ቸ​ውም በላይ ከአ​ለው ጠፈር በላይ የሰ​ን​ፔር ድን​ጋይ የሚ​መ​ስል የዙ​ፋን አም​ሳያ ነበረ፤ በዙ​ፋ​ኑም አም​ሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አም​ሳያ ነበረ።


በዝ​ናብ ቀን በደ​መና ውስጥ እንደ አለ ቀስተ ደመና አም​ሳያ፥ እን​ዲሁ በዙ​ሪ​ያው ያለ ፀዳል አም​ሳያ ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ምሳሌ መልክ ይህ ነበረ። በአ​የ​ሁም ጊዜ በግ​ን​ባሬ ተደ​ፋሁ። የሚ​ና​ገ​ር​ንም ድምፅ ሰማሁ።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም በኪ​ሩ​ቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር በላ​ያ​ቸው እንደ ሰን​ፔር ድን​ጋይ ያለ ዙፋን የሚ​መ​ስል መልክ ተገ​ለጠ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት በዔ​ድን ነበ​ርህ፤ የከ​በረ ዕን​ቍስ ሁሉ፥ ሰር​ድ​ዮን፥ ቶጳ​ዝ​ዮን፥ አል​ማዝ፥ ቢረሌ፥ መረ​ግድ፥ ኢያ​ሰ​ጲድ፥ ሰን​ፔር፥ በሉር፥ የሚ​ያ​ብ​ረ​ቀ​ርቅ ዕንቍ፥ ወር​ቅም ልብ​ስህ ነበረ፤ የከ​በ​ሮ​ህና የእ​ን​ቢ​ል​ታህ ሥራ በአ​ንተ ዘንድ ነበረ፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​በ​ትም ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ነበር።


ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፤