የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 93:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተበ​ቃይ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ልጥ ተበ​ቃይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ነገሠ፥ ግርማን ተጐናጸፈ፥ ጌታ ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፥ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ንጉሥ ነው፤ ግርማንና ኀይልን ተጐናጽፎአል፤ ምድርን በአንድ ስፍራ አጸናት፤ ከቶም አትናወጥም።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 93:1
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምድር ሁሉ በፊቱ ትነ​ዋ​ወ​ጣ​ለች፤ ዓለ​ም​ንም እን​ዳ​ት​ነ​ዋ​ወጥ አጸ​ናት።


ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፥ ምድ​ርም ሐሤ​ትን ታድ​ርግ፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገሠ” በሉ።


ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትና ክብር ከአ​ንተ ዘንድ ነው፤ አቤቱ፥ አን​ተም ሁሉን ትገ​ዛ​ለህ፤ የሥ​ል​ጣን ሁሉ ጌታ ነህ፤ ኀይ​ልና ብር​ታት በእ​ጅህ ነው፤ ኀያል ነህ፤ ታላቅ ለማ​ድ​ረግ፥ ለሁ​ሉም ኀይ​ልን ለመ​ስ​ጠት ዓለ​ምን ሁሉ በእ​ጅህ የያ​ዝህ ነህ።


እስኪ ልዕ​ል​ና​ንና ኀይ​ልን ተላ​በስ፤ በክ​ብ​ርና በግ​ር​ማም ተጐ​ና​ጸፍ።


ጨረ​ቃን በጊ​ዜው ፈጠ​ርህ፤ ፀሐ​ይም መግ​ቢ​ያ​ውን ያው​ቃል።


ባሕ​ርን የብስ አደ​ረ​ጋት፥ ወን​ዙ​ንም በእ​ግር ተሻ​ገሩ፤ በዚያ በእ​ርሱ ደስ ይለ​ናል።


በኀ​ይሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዛል፤ ዐይ​ኖቹ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ የም​ታ​ውቁ ራሳ​ች​ሁን ከፍ ከፍ አታ​ድ​ርጉ።


በዚ​ያም የቀ​ስ​ትን ኀይል፥ ጋሻን፥ ጦር​ንና ሰል​ፍ​ንም ሰበረ፤ በዚ​ያም ቀን​ዶ​ችን ሰበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ወ​ድዱ፥ ክፋ​ትን ጥሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጻ​ድ​ቃ​ኑን ነፍ​ሶች ይጠ​ብ​ቃል፥ ከኃ​ጥ​ኣ​ንም እጅ ያድ​ና​ቸ​ዋል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ፥ የቀኙ ማዳን፥ የተ​ቀ​ደሰ ክን​ዱም ድንቅ ነውና።


በም​ድር ሁሉ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ፥


ወገ​ቡን በጽ​ድቅ ይታ​ጠ​ቃል፤ እው​ነ​ት​ንም በጎኑ ይጐ​ና​ጸ​ፋል።


እኔ ምድ​ርን ሠር​ቻ​ለሁ፤ ሰው​ንም በእ​ር​ስዋ ላይ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማ​ያ​ትን አጽ​ን​ቼ​አ​ለሁ፤ ከዋ​ክ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አዝ​ዣ​ለሁ።


ሰማ​ይን የፈ​ጠረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እር​ሱም ምድ​ርን የሠ​ራና ያደ​ረገ ያጸ​ና​ትም፥ መኖ​ሪ​ያም ልት​ሆን እንጂ ለከ​ንቱ እን​ድ​ት​ሆን ያል​ፈ​ጠ​ራት አም​ላክ፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ዕለት ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ድኅ​ነት በሚ​ደ​ረ​ግ​በ​ትም ቀን ረድ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ቃል ኪዳን አድ​ርጌ ለሕ​ዝቡ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆ​ኑ​ትን ርስ​ቶች ትወ​ርስ ዘንድ፤


ቃሌን በአ​ፍሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ሰማ​ይን በዘ​ረ​ጋ​ሁ​በ​ትና ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ት​ሁ​በት በእጄ ጥላ እጋ​ር​ድ​ሻ​ለሁ፤ ጽዮ​ን​ንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላ​ታ​ለሁ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ የክ​ን​ድ​ሽ​ንም ኀይል ልበሺ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ዘመን እንደ ጥንቱ ትው​ልድ ተነሺ።


ሰላ​ምን የሚ​ያ​ወራ፥ መል​ካም የም​ሥ​ራ​ች​ንም የሚ​ና​ገር፥ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም የሚ​ያ​ወራ፥ ጽዮ​ን​ንም፥ “አም​ላ​ክሽ ነግ​ሦ​አል” የሚል ሰው እግሩ በተ​ራ​ሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።


ጽድ​ቅ​ንም እንደ ጥሩር ለበሰ፤ በራ​ሱም ላይ የማ​ዳ​ንን ራስ ቍር አደ​ረገ፤ የበ​ቀ​ል​ንም ልብስ ለበሰ።


ከኤ​ዶ​ም​ያስ፥ ከባ​ሶራ የሚ​መጣ፥ ልብ​ሱም የቀላ፥ የሚ​መካ ኀይ​ለኛ፥ አለ​ባ​በ​ሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የም​ከ​ራ​ከር፥ ስለ ማዳ​ንም የም​ፈ​ርድ እኔ ነኝ።


ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


ስለ ልጁ ግን፥ “ጌታ ሆይ፥ ዙፋ​ንህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በት​ርም የጽ​ድቅ በትር ነው” አለ።


እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።