ባሕርን የብስ አደረጋት፥ ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፤ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል።
ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤ ኀይልንም ታጥቀሃል።
በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ በጽድቅ፥ በድንቅ ነገሮች መለስክልን።
በኀይልህ ተራራዎችን አጽንተሃል፤ ብርታትንም ታጥቀሃል።
አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለም አልፈር፤ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
ጌታ እግዚአብሔር ተበቃይ ነው፥ እግዚአብሔር በግልጥ ተበቃይ ነው።
እነሆ፥ አምላኬ መድኀኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ክብሬና ዝማሬዬ ነው፤ መድኀኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜአለሁ፤ አልፈራምም።”
እናንተ በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ተመለሱ፤ ትድኑማላችሁ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ የክንድሽንም ኀይል ልበሺ፤ እንደ ቀድሞውም ዘመን እንደ ጥንቱ ትውልድ ተነሺ።
ከኤዶምያስ፥ ከባሶራ የሚመጣ፥ ልብሱም የቀላ፥ የሚመካ ኀይለኛ፥ አለባበሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የምከራከር፥ ስለ ማዳንም የምፈርድ እኔ ነኝ።
ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።
ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።
የኀያላንን ቀስት ሰብሮአል፤ ደካሞችንም ኀይልን አስታጥቋቸዋል።