መዝሙር 37:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ባላጋራ ሆኑኝ፥ ከበውም ደበደቡኝ፥ ዘመዶቼም ተስፋ ቈርጠው ተለዩኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትሑቶች ምድርን ይወርሳሉ፤ ብልጽግናንና ሰላምን በማግኘት ይደሰታሉ። |
በችግርሽ ቀን በጮኽሽ ጊዜ እስኪ ይታደጉሽ፤ እነሆ፥ ዐውሎ ይወስዳቸዋል፤ ነፋስም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። ወደ እኔ የሚጠጉ ግን ምድሪቱን ይገዛሉ፤ የተቀደሰውን ተራራዬንም ይወርሳሉ።
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም፤ ልባችሁ አይደንግጥ፤ አትፍሩም።
በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”
ሁሉ የሚገኝባት፥ ከልቡናና ከአሳብ ሁሉ በላይ የምትሆን የእግዚአብሔር ሰላም በኢየሱስ ክርስቶስ ልባችሁንና አሳባችሁን ታጽናው።