ተናገረ፥ አንበጣም፥ ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ መጣ፥
እኔ በእግዚአብሔር ደስ እንደሚለኝ፣ የልቤ ሐሳብ እርሱን ደስ ያሠኘው።
ቃሌ ለእርሱ ይጣፍጠው፥ እኔም በጌታ ደስ ይለኛል።
ደስታዬ በእርሱ ስለ ሆነ እርሱም በማቀርብለት የተመስጦ ጸሎት ደስ ይበለው።
ይስሐቅም በመሸ ጊዜ በልቡ እያሰላሰለ ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር፤ ዓይኖቹንም አቀና፤ እነሆም ግመሎች ሲመጡ አየ።
የእግዚአብሔር ሕግ ብቻ ፈቃዱ የሆነ፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያስብ፥
ፍርድን የሚጠብቁ፥ ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው።
የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ የልቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
በግብጽ ሀገርና በጣኔዎስ በረሃ በአባቶቻቸው ፊት የሠራውን ተአምራት።
በአንተ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትንም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።
እንዲሁም ጥበብን በሰውነትህ ተማር፥ ብታገኛት ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም።
ልቡናዬም በአምላኬ በመድኀኒቴ ሐሤት ታደርጋለች።
ዘወትር በጌታችን ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላችኋለሁ፦ ደስ ይበላችሁ።
ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ።