የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 35:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ከተ​ሞ​ችን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ስድ​ስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚ​ሸ​ሽ​ባ​ቸው የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ናቸው፤ ከእ​ነ​ዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተ​ሞ​ችን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ለሌዋውያኑ ከምትሰጧቸው ከተሞች ስድስቱ፣ ሰው የገደለ ሸሽቶ የሚጠጋባቸው መማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞች ስጧቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለሌዋውያንም የምትሰጡአቸው ስድስቱ የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ እነርሱም ነፍሰ ገዳይ እንዲሸሽባቸው የምትሰጡአቸው ናቸው፤ ከእነዚህም ሌላ አርባ ሁለት ከተሞች ትሰጣላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ማናቸውም ሰው፥ በስሕተት ሰውን ቢገድል ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ስድስት ከተሞችን ለሌዋውያን ትሰጣላችሁ፤ በተጨማሪም አርባ ሁለት ከተሞችን፥

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለሌዋውያንም የምትሰጡአቸው ስድስቱ የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ እነርሱም ነፍሰ ገዳይ ይሸሽባቸው ዘንድ የምትሰጡአቸው ናቸው፤ ከእነዚህም ሌላ አርባ ሁለት ከተሞች ትሰጣላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 35:6
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለድ​ሆች መጠ​ጊያ ሆና​ቸው፥ እር​ሱም በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ረዳ​ታ​ቸው ነው።


ሳይ​ፈ​ቅድ ቢመ​ታው፥ ባይ​ሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ገት በእጁ ቢጥ​ለው፥ ገዳዩ የሚ​ሸ​ሽ​በ​ትን ስፍራ እኔ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ።


ከሙ​ቀት ለጥላ፥ ከዐ​ውሎ ነፋ​ስና ከዝ​ና​ብም ለመ​ጠ​ጊ​ያና ለመ​ሸ​ሸ​ጊያ ጎጆ ይሆ​ናል።


ከከ​ተ​ማው ውጭ በም​ሥ​ራቅ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በደ​ቡብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በም​ዕ​ራብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በሰ​ሜ​ንም በኩል ሁለት ሺህ ክንድ ትከ​ነ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ከተ​ማ​ውም በመ​ካ​ከል ይሆ​ናል፤ ይህም የከ​ተ​ሞቹ መሰ​ማ​ርያ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።


እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።


ለካ​ህ​ኑም ለአ​ሮን ልጆች እነ​ዚ​ህን ሰጡ፤ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ኬብ​ሮ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሌም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥


ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ሴኬ​ም​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ጌዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገ​ኖች ለጌ​ድ​ሶን ልጆች ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ በባ​ሳን ውስጥ የሆ​ነ​ች​ውን ጎላ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሁለ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከር​ስ​ታ​ቸው እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ​አ​ቸው።


ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ሊላ ውስጥ ቃዴ​ስ​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኤማ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃር​ቴ​ን​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዋን፤ ሦስ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል ከሮ​ቤል ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ በሚ​ሶን ምድረ በዳ ቦሶ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤


ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤