ዘኍል 31:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነዚያም ከተዋጉት፥ ወደ ሰልፍም ከወጡት ሰልፈኞች ዘንድ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከአምስት መቶ አንድ ለእግዚአብሔር ግብር ታወጣላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጦርነቱ ከተካፈሉት ወታደሮች ድርሻ ላይ፣ ከሰውም ሆነ ከቀንድ ከብት፣ ከአህያ፣ ከበግ ወይም ከፍየል ከየዐምስት መቶው አንዱን ለእግዚአብሔር ግብር አውጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነዚያም ወደ ጦርነት ወጥተው ከተዋጉት ወታደሮች ድርሻ፥ ከሰዎችም ከበሬዎችም ከአህዮችም ከበጎችም ከአምስት መቶ አንድ ለጌታ ግብር አውጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለወታደሮቹ ከተመደበው ክፍል፥ ከአምስት መቶ እስረኞች አንዱን፥ እንዲሁም ከከብቱ፥ ከአህዮቹ፥ ከበጎቹና ከፍየሎቹ ከአምስት መቶው አንዱን እጅ ለእኔ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ ለዩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነዚያም ከተዋጉት ወደ ሰልፍም ከወጡት ሰልፈኞች ዘንድ፥ ከሰዎችም ከበሬዎችም ከአህዮችም ከመንጎችም ከአምስት መቶ አንድ ለእግዚአብሔር ግብር አውጣ። |
ንጉሡም ዳዊት ከአሕዛብ ሁሉ ከኤዶምና ከሞዓብ፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከፍልስጥኤማውያንም፥ ከአማሌቅም ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ደግሞ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
በዚያ ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከተዋረደና ከደከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለዓለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚያደርግና ከሚረገጥ፥ በሀገሩ ወንዝ ዳር ከሚኖር ሕዝብ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም በተጠራበት በደብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀርባል።
ንግድዋና ዋጋዋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ንግድዋም በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩ ለመብላትና ለመጠጣት፥ ለመጥገብም፥ በእግዚአብሔርም ፊት ለመታሰቢያ ይሆናል እንጂ ለእነርሱ አይሰበሰብም።
ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ የተርሴስም መርከቦች አስቀድመው ይመጣሉ፤ ልጆችሽ ስለ ከበረው ስለ እስራኤል ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ስም ወርቅና ብር ይዘው ከሩቅ ሀገር ይመጣሉ።
“ለሌዊም ልጆች እነሆ፥ በምስክሩ ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ዐሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።
“ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ከእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን ዐሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ እናንተምከእርሱ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ የዐሥራት ዐሥራት ታቀርባላችሁ።
ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ እኩሌታ፥ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከእንስሶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፤ የእግዚአብሔርንም ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።”
ሙሴ ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ከሰውና ከእንስሳ ከሃምሳ አንድ ወሰደ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ።
ነገር ግን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ የናስና የብረትም ዕቃ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን፤ ወደ እግዚአብሔርም ግምጃ ቤት ይግባ።”
ከተማዪቱንም፥ በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፤ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን፥ የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ።
በዚያም ቀን ኢያሱ እነርሱን ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቈራጮችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው። ስለዚህም የገባዖን ሰዎች ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ እግዚአብሔርም ለመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ቈራጮች፥ ውኃም ቀጂዎች ሆኑ።