እንደ ተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዐቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ።
ዘኍል 29:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ዐሥራ ሦስት በሬዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ዐሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ ሦስት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ እንዲያሰኝ በእሳት አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ዐሥራ ሦስት ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ዐሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ በመጀመሪያው ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ዐሥራ ሦስት ወይፈኖች፥ ሁለት የበግ አውራዎች፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን አድርጋችሁ አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔርም ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አሥራ ሦስት ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ አሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑ። |
እንደ ተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዐቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ።
“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
“በወሩም መባቻ ለእግዚአሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥
በእሳትም የተደረገውን ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት በሬዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነውር የሌለባቸው ይሁኑላችሁ።
ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት በሬዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥
“በሰባተኛውም ወር ዐሥራ አምስተኛዋ ቀን ለእናንተ የተቀደሰች ትሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት፤ ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር በዓል አድርጉ።
ለእህል ቍርባናቸውም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለዐሥራ ሦስት በሬዎች ለእያንዳንዱ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለሁለቱ አውራ በጎች ለእያንዳንዱ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥
ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ከላሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት፥ የበግ ጠቦቶች፥
ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ፥ ከላሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑላችሁ።
ወንድሞቻችን፥ ሰውነታችሁን ለእግዚአብሔር ሕያውና ቅዱስ፥ ደስ የሚያሰኝም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እማልዳችኋለሁ። ይህም በዕውቀት የሚሆን አገልግሎታችሁ ነው።