የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ነህምያ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ስ​ናሃ ልጆ​ችም የዓሣ በር ሠሩ፤ ሠረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም አኖሩ፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የዓሣ በሩን የሃስናአ ልጆች ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የስናአ ልጆች “የዓሣ በር” ሠሩ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ በሮቹን አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም ሠሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሃስናአ ጐሣ አባሎች የዓሣ ቅጽር በር የተባለውን ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም መዝጊያ፥ መወርወሪያና ቊልፎችን አበጁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሃስናአ ልጆችም የዓሣ በር ሠሩ፥ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት



ነህምያ 3:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ዓለ​ምን ሁሉ የም​ት​ገዛ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም የጻ​ድ​ቃን ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ ሆይ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ከዓ​ለ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር የፈ​ጠ​ርህ፥


የሴ​ዓ​ናህ ልጆች ሦስት ሺህ ስድ​ስት መቶ ሠላሳ።


ከኤ​ፍ​ሬ​ምም በር በላይ፥ በአ​ሮ​ጌው በርና በዓሣ በር፥ በአ​ና​ን​ኤ​ልም ግንብ፥ በሃ​ሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘ​በ​ኞ​ችም በር አጠ​ገብ ቆሙ።


በቤ​ቱም አጠ​ገብ ላለው ለግ​ንብ በሮች፥ ለከ​ተ​ማ​ውም ቅጥር፥ ለም​ገ​ባ​በ​ትም ቤት እን​ጨት እን​ዲ​ሰ​ጠኝ ለን​ጉሡ ዱር ጠባቂ ለአ​ሳፍ ደብ​ዳቤ ይሰ​ጠኝ” አል​ሁት። ንጉ​ሡም ሁሉን ሰጠኝ። የከ​በ​ረች የአ​ም​ላኬ እጅ ከእኔ ጋር ነበ​ረ​ችና።


በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የሜ​ሴ​ዜ​ቤል ልጅ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የበ​ሃና ልጅ ሳዶቅ ይሠራ ጀመረ።


የፋ​ሴሓ ልጅ ኢዮ​ዳ​ሄና የበ​ሶ​ድያ ልጅ ሜሱ​ላም አሮ​ጌ​ውን በር አደሱ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹን አኖሩ፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥ​ሩን እንደ ሠራሁ፥ ከፍ​ራ​ሹም አን​ዳች እን​ዳ​ል​ቀ​ረ​በት ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦቢያ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም የቀ​ሩ​ትም ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሰሙ፤ ነገር ግን እስ​ከ​ዚያ ጊዜ ድረስ በበ​ሮቹ ውስጥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አላ​ቆ​ም​ሁም ነበር።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተ​ሠራ በኋላ፥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አቆ​ምሁ፤ በረ​ኞ​ቹ​ንና መዘ​ም​ራ​ኑን፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ሾምሁ፤


የሴ​ናዓ ልጆች ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ።


በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ከዓሣው በር የጩኸት ድምፅ፥ ከከተማውም በሁለተኛው ክፍል ውካታ፥ ከኮረብቶቹም ታላቅ ሽብር ይሆናል።