የቀረውም የሕዝቅያስ ነገር፥ ኀይሉም ሁሉ፥ ኵሬውንና መስኖውን እንደ ሠራ፥ ውኃውንም ወደ ከተማዪቱ እንዳመጣ፥ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
ነህምያ 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ የቤሶር ግዛት እኩሌታ ገዢ የዓዛቡህ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር አንጻር እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራውም መዋኛ፥ እስከ ኀያላኑም ቤት ድረስ ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዥ የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር ትይዩ እስከ ሰው ሠራሹ ኵሬና የጀግኖች ቤት ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን መልሶ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር ፊት ለፊት እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራው መዋኛ ስፍራና እስከ ኃያላኑ ቤት ድረስ አደሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የነበረው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር (ከዳዊት መቃብር ትይዩ ጀምሮ)፥ እስከ ኩሬ፤ እስከ ጀግኖች ሰፈር ድረስ ያለውን ክፍል ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ የቤትጹር ግዛት እኩሌታ አለቃ የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር አንጻር እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራውም መዋኛ፥ እስከ ኃያላኑም ቤት ድረስ አደሰ። |
የቀረውም የሕዝቅያስ ነገር፥ ኀይሉም ሁሉ፥ ኵሬውንና መስኖውን እንደ ሠራ፥ ውኃውንም ወደ ከተማዪቱ እንዳመጣ፥ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቱ በተሞላ አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የቀብር ሥርዐት አደረጉለት።
የቤትሐካሪምም ግዛት ገዢ የሬካብ ልጅ መልክያ ከወንድሞቹና ከልጆቹ ጋር የጕድፍ መጣያውን በር ሠራ፤ ከደነው፤ ሳንቃዎቹንም አቆመ፤ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ።
ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሁም ሠሩ። በአጠገባቸውም የቅዒላ ግዛት እኩሌታና የአውራጃዎችዋ ገዢ አሰብያ ሠራ።
በአሮጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፤ ቀድሞ የሠራውንም አላያችሁም።
እግዚአብሔርም ኢሳይያስን አለው፥ “አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው መታጠቢያ ቦታ ውጡ፤
“እናንተ ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት ነገር እንደ ሞተ እንደ ተቀበረም፥ መቃብሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደ አለ ገልጬ እንድነግራችሁ ትፈቅዱልኛላችሁን?