የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ነህምያ 13:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም መጣሁ፤ ኤል​ያ​ሴ​ብም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ለጦ​ቢያ ዕቃ ቤቱን በማ​ዘ​ጋ​ጀት ያደ​ረ​ገ​ውን ክፉ ነገር አስ​ተ​ዋ​ልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ኢየሩሳሌም ተመለስሁ፤ በዚያም ኤልያሴብ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ለጦቢያ አንድ መኖሪያ ክፍል በመስጠት የፈጸመውን ክፉ ድርጊት ተረዳሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ኢየሩሳሌምም መጣሁ፥ ኤልያሺብ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ለጦብያ ጓዳውን በማዘጋጀት ያደረገውን ክፉ ነገር አስተዋልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ ኢየሩሳሌም ተመለስኩ፤ እዚያም እንደ ደረስኩ ኤልያሺብ ለጦቢያ በቤተ መቅደሱ ግቢ ውስጥ አንድ መኖሪያ ክፍል የፈቀደለት መሆኑን ሰማሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ኢየሩሳሌምም መጣሁ፥ ኤልያሴብም በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ለጦብያ ጓዳውን በማዘጋጀት ያደረገውን ክፉ ነገር አስተዋልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ነህምያ 13:7
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የኤ​ል​ዮ​ዔ​ና​ኢም ልጆች አዳ​ይያ፥ ኤል​ያ​ሴብ፥ ፈላያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐ​ናን፥ ዶላያ፥ ዓናኒ ሰባት ነበሩ።


ይህም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ የሕ​ዝቡ አለ​ቆች ወደ እኔ ቀር​በው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ እንደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ እንደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ እንደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፦ እንደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ እንደ አሞ​ና​ው​ያን፥ እንደ ሞዓ​ባ​ው​ያን፥ እንደ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንና እንደ አሞ​ራ​ው​ያን ርኵ​ሰት ያደ​ር​ጋሉ እንጂ ከም​ድር አሕ​ዛብ አል​ተ​ለ​ዩም፤


በዚ​ያም ቀን የሙ​ሴን መጽ​ሐፍ በሕ​ዝቡ ጆሮ አነ​በቡ፤ አሞ​ና​ው​ያ​ንና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ገቡ የሚል በዚያ አገኙ።


ለሌ​ዋ​ው​ያን፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ንና ለበ​ረ​ኞቹ እንደ ሕጉ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት፥ ለካ​ህ​ና​ቱም የሆ​ነ​ውን ቀዳ​ም​ያ​ቱን አስ​ቀ​ድሞ ያስ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ለት ነበር።


ዮድ። አስ​ጨ​ና​ቂው በም​ኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባ​ኤህ እን​ዳ​ይ​ገቡ ያዘ​ዝ​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ወደ መቅ​ደ​ስዋ ሲገቡ አይ​ታ​ለ​ችና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ! እን​ደ​ም​ት​ጣ​ሉና እን​ደ​ም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከቀ​ሎ​ኤስ ወገ​ኖች ስለ እና​ንተ ነገ​ሩኝ።