የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ማኅ​በ​ሩ​ንም ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሰበ​ሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም ጌታ እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ሕዝቡም ተሰበሰበ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩ ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰቡ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 8:4
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቀ​ረ​ውም የመባ ወርቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሠ​ሩ​በት ዘንድ ንዋየ ቅድ​ሳት ሆኖ ተሠራ። ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም ከቀይ ግም​ጃም ለመ​ቅ​ደሱ አገ​ል​ግ​ሎት ልብ​ሶ​ችን ሠሩ፤ እን​ዲ​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለአ​ሮን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ልብስ ሠሩ።


ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓው በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለ​ፈው ከመ​ደ​ረ​ቢ​ያው ቋድ በላይ እን​ዲ​ሆን፥ ከመ​ደ​ረ​ቢ​ያው እን​ዳ​ይ​ለይ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከቀ​ለ​በ​ቶቹ ጋር ወደ መደ​ረ​ቢ​ያው ቀለ​በ​ቶች በሰ​ማ​ያዊ ፈትል አሰ​ሩት።


በቀ​ሚሱ ዘርፍ ዙሪያ ሻኵ​ራ​ንና ሮማ​ንን፥ ሻኩ​ራ​ንና ሮማ​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለማ​ገ​ል​ገል አደ​ረጉ።


ከተ​ፈ​ተ​ለም ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እር​ስ​ዋን ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀይ ግም​ጃም፥ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም እንደ ሠሩ የል​ብሰ መት​ከ​ፉን ቋድ ሠሩ።


ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የመ​ታ​ሰ​ቢያ ድን​ጋ​ዮች ይሆኑ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ አደ​ረ​ጓ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ የአ​ሮ​ንን ልጆች አቀ​ረበ፤ የበ​ፍታ ቀሚ​ሶ​ች​ንም አለ​በ​ሳ​ቸው፤ በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም አስ​ታ​ጠ​ቃ​ቸው፤ አክ​ሊ​ልም ደፋ​ላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ወይ​ፈ​ኑን፥ ቍር​በ​ቱ​ንም፥ ሥጋ​ው​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም ከሰ​ፈሩ ውጭ በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


ሙሴም ከቅ​ድ​ስ​ናው አውራ በግ ፍር​ም​ባ​ውን ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በው ዘንድ ቈራ​ረጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ይህ ለቅ​ድ​ስና ከታ​ረ​ደው አውራ በግ የሙሴ እድል ፈንታ ሆነ።


ማኅ​በ​ሩ​ንም ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሰብ​ስ​ባ​ቸው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አዝ​ዞ​ኛ​ልና እን​ዳ​ት​ሞቱ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሌሊ​ቱ​ንና ቀኑን ሰባት ቀን ተቀ​መጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐት ጠብቁ፤”


ሙሴም ማኅ​በ​ሩን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታደ​ርጉ ዘንድ ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው” አላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በራሱ ላይ አክ​ሊል አደ​ረ​ገ​ለት፤ በአ​ክ​ሊ​ሉም ላይ በፊቱ በኩል የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን የወ​ርቅ መር​ገፍ አደ​ረገ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተማ​ርሁ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እር​ሱን ራሱን በያ​ዙ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ኅብ​ስ​ቱን አነሣ።


እኔ የተ​ማ​ር​ሁ​ትን አስ​ቀ​ድሜ መጽ​ሐፍ እን​ደ​ሚል እን​ዲህ ብዬ አስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ፥ “ክር​ስ​ቶስ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ሞተ።


“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ሁሉ ታደ​ር​ገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእ​ርሱ ላይ አት​ጨ​ምር፤ ከእ​ር​ሱም ምንም አታ​ጕ​ድል።