የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘እጅግ ቅዱስ የሆነው የበደል መሥዋዕት የአቀራረብ ሥርዐት ይህ ነው፦

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“የበደል መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እጅግ የተቀደሰ ስለ ሆነው የበደል ስርየት መሥዋዕት አቀራረብ የተሰጠው መመሪያ ይህ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የበደል መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 7:1
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሌ​ዋ​ዊ​ውም የይ​ም​ላእ ልጅ የም​ሥ​ራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መባና የተ​ቀ​ደ​ሱ​ትን ነገ​ሮች እን​ዲ​ያ​ካ​ፍል ሕዝቡ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ቀ​ረ​ቡት ላይ ተሾመ።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንና የበ​ደ​ሉ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ያር​ዱ​ባ​ቸው ዘንድ፥ በበሩ ደጀ ሰላም በዚህ ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች፥ በዚ​ያም ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ።


የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት የን​ስ​ሓ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ይበ​ላሉ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ እርም የሆ​ነው ነገር ሁሉ ለእ​ነ​ርሱ ይሆ​ናል።


እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ካህ​ናቱ ሕዝ​ቡን ለመ​ቀ​ደስ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ እን​ዳ​ይ​ወጡ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​በ​ስ​ሉ​በት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ጋ​ግ​ሩ​በት ስፍራ ይህ ነው።”


የቅ​ዱ​ሱ​ንና የቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳ​ኑን የአ​ም​ላ​ኩን መባ ይብላ፤


“ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ለማ​ም​ጣት ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና ዘይት አያ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦


“ሰው ቢዘ​ነጋ፥ ሳያ​ው​ቅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ቀ​ደ​ሰው በማ​ና​ቸ​ውም ነገር ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ን​ጋዉ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።


“ስለ ሠራው ኀጢ​አት የበግ መግዣ ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው ግን፥ ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል። ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤


ካህ​ኑም አስ​ቀ​ድሞ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ያቀ​ር​ባል፤ ራሱ​ንም ከአ​ን​ገቱ ይቆ​ለ​ም​መ​ዋል፤ ነገር ግን አይ​ቈ​ር​ጠ​ውም።


በእ​ርሾ ቦክቶ አይ​ጋ​ገ​ርም። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የሰ​ጠ​ኋ​ቸው ዕድል ፈንታ ይህ ነው፤ እር​ሱም እንደ ኀጢ​አ​ትና እንደ በደል መሥ​ዋ​ዕት ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


“አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ታ​ረ​ድ​በት ስፍራ የኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታ​ረ​ዳል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


በስ​እ​ለቱ ወራ​ትም ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቀ​ደ​ሳል፤ የአ​ንድ ዓመ​ትም ተባት ጠቦት ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ያምጣ፤ ስእ​ለቱ ግን ረክ​ሶ​አ​ልና ያለ​ፈው ወራት ሁሉ አይ​ቈ​ጠ​ር​ለ​ትም።