የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ተቀ​ብቶ የተ​ሾ​መው ካህን ከወ​ይ​ፈኑ ደም በእጁ ወስዶ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ያመ​ጣ​ዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም ጥቂት ወስዶ ወደ መገናኛው ድንኳን ይግባ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የተቀባውም ካህን ከወይፈኑ ደም ወስዶ ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ከኰርማው ደም ጥቂት ወስዶ ወደ ድንኳኑ በማስገባት፥

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የተቀባውም ካህን ከወይፈኑ ደም ወስዶ ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 4:5
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም ወስዶ በስ​ር​የቱ መክ​ደኛ ላይ ወደ ምሥ​ራቅ በጣቱ ይረ​ጨ​ዋል፤ ከደ​ሙም በመ​ክ​ደ​ኛው ፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረ​ጫል።


“ስለ ሕዝ​ቡም ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ያር​ዳል፤ ደሙ​ንም ወደ መጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም ደም እን​ዳ​ደ​ረገ በፍ​የሉ ደም ያደ​ር​ጋል፤ በመ​ክ​ደ​ኛው ላይና በመ​ክ​ደ​ኛው ፊት ይረ​ጨ​ዋል።


ከደ​ሙም በእ​ርሱ ላይ ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረ​ጫል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ርኩ​ስ​ነት ያነ​ጻ​ዋል፤ ይቀ​ድ​ሰ​ው​ማል።


የተ​ቀ​ባ​ውም ሊቀ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ላይ በደል እን​ዲ​ቈ​ጠ​ር​ባ​ቸው ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢ​አቱ ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​በ​ዋል።


ካህ​ና​ትም የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ ፈጽሞ ይቃ​ጠ​ላል፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች አይ​በ​ላም።”


አል​ዓ​ዛ​ርም ከደ​ምዋ በጣቱ ይወ​ስ​ዳል፤ ከደ​ም​ዋም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ሰባት ጊዜ ይረ​ጫል።


ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።