የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ማና​ቸ​ውም ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ቢሳል አንተ እን​ደ​ም​ት​ገ​ም​ተው መጠን ስለ ሰው​ነቱ ዋጋ​ውን ይስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ማንኛውም ሰው ተመጣጣኙን ዋጋ በመክፈል ለእግዚአብሔር ሰውን ለመስጠት የተለየ ስእለት ቢሳል፣

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ማናቸውም ሰው ሰውን ለጌታ ሊሰጥ ቢሳል፥ አንተ እንደምትገምተው መጠን ስለ ሰው ተመጣጣኝ የሆነውን ዋጋ ይስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ተስሎ ሲፈጸምለት፥ ያ የተሳለው ስለት ሰውን ለመስጠት ከሆነ የመዋጀት ዋጋው እንደ ገመትከው ሆኖ እንደሚከተለው ይሁን፦

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሰውን ለእግዚአብሔር ሊሰጥ ቢሳል አንተ እንደምትገምተው መጠን ስለ ሰው ዋጋውን ይስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 27:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ከሚ​ያ​መ​ጣው ካህ​ናቱ ለራ​ሳ​ቸው ይው​ሰዱ፤ በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ይጠ​ግ​ኑ​በት” አላ​ቸው።


ሕልም በብዙ መከራ፥ እን​ዲ​ሁም የሰ​ነፍ ቃል በብዙ ነገር ይመ​ጣ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እስ​ራ​ኤ​ልም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ይህን ሕዝብ አሳ​ል​ፈህ በእ​ጃ​ችን ብት​ሰ​ጠን እር​ሱ​ንና ከተ​ሞ​ቹን ሕርም ብለን እና​ጠ​ፋ​ዋ​ለን” ብለው ስእ​ለት ተሳሉ።


ሴትም ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ብት​ሳል፥ እር​ስ​ዋም በአ​ባቷ ቤት ሳለች በብ​ላ​ቴ​ን​ነቷ ጊዜ ራስ​ዋን ብት​ለይ፥


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ያደ​ርግ ዘንድ ልዩ ስእ​ለት ቢሳል፥


“ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ እርሻ በገ​ባህ ጊዜ እሸ​ቱን በእ​ጅህ ቀጥ​ፈህ ብላ፤ ወዳ​ል​ታ​ጨ​ደው ወደ ባል​ን​ጀ​ራህ እህል ግን ማጭድ አታ​ግባ።


ሁለት ወርም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ወደ አባቷ ተመ​ለ​ሰች፤ ዮፍ​ታ​ሔም የተ​ሳ​ለ​ውን ስእ​ለት አደ​ረገ፤ እር​ስ​ዋም ወንድ አላ​ወ​ቀ​ችም ነበር።


እር​ስ​ዋም፥ “አዶ​ናይ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! የባ​ር​ያ​ህን መዋ​ረድ ተመ​ል​ክ​ተህ ብታ​ስ​በኝ፥ ለባ​ር​ያ​ህም ወንድ ልጅ ብት​ሰጥ ዕድ​ሜ​ውን ሁሉ ለአ​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥም አይ​ጠ​ጣም። ምላ​ጭም በራሱ ላይ አይ​ደ​ር​ስም” ብላ ስእ​ለት ተሳ​ለች።


እኔም ደግሞ ዕድ​ሜ​ውን ሙሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግል ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።”