የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቍር​ባ​ን​ህም በመ​ቀ​ቀያ የበ​ሰለ ቍር​ባን ቢሆን፥ ዘይት የገ​ባ​በት ከመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት የተ​ደ​ረገ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእህል ቍርባንህ በመጥበሻ የሚበስል ከሆነ፣ ከላመ ዱቄትና ከዘይት ይዘጋጅ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቁርባንህም በመጥበሻ የተጋገረ የእህል ቁርባን ቢሆን፥ ዘይት የገባበት ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መባው በመጥበሻ የተጋገረ ቂጣ ከሆነ የወይራ ዘይት ተጨምሮበት ከተለወሰ የላመ ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቍርባንህም በመቀቀያ የበሰለ የእህል ቍርባን ቢሆን፥ ዘይት የገባበት ከመልካም ዱቄት የተደረገ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 2:7
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግ​ሞም ገጸ ኅብ​ስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በም​ጣ​ድም ቢጋ​ገር፥ ቢለ​ወ​ስም ለእ​ህል ቍር​ባን በሆ​ነው በመ​ል​ካሙ ዱቄት በመ​ስ​ፈ​ሪ​ያና በልክ ሁሉ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


ቈር​ሰ​ህም ዘይት ታፈ​ስ​ስ​በ​ታ​ለህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ነው።


ከዚ​ህም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመ​ጣ​ለህ፤ ወደ ካህ​ኑም ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ፤ ካህ​ኑም ወደ መሠ​ዊ​ያው ያቀ​ር​በ​ዋል።


በእ​ቶን የተ​ጋ​ገ​ረው የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ፥ በመ​ቀ​ቀ​ያም ወይም በም​ጣድ የበ​ሰ​ለው ሁሉ ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ካህን ይሆ​ናል።