የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 18:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ኅ​ት​ህን ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ባ​ትህ ልጅ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ በቤት ወይም በውጭ የተ​ወ​ለ​ደች ብት​ሆን፥ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ከእኅትህ ጋራ ግብረ ሥጋ አትፈጽም፤ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፣ ከአባትህ ወይም ከእናትህ ሴት ልጅ ጋራ በግብረ ሥጋ አትገናኝ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእኅትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ፥ በአገር ቤት ወይም በውጭ አገር የተወለደች ብትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእኅትህ ጋር የፍትወተ ሥጋ ግንኙነት አታድርግ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የናትህ ልጅ፥ በቤት ወይም በውጪ የተወለደች ብትሆን ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእኅትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ፥ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 18:9
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰውም ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ሚስት ጋር ሰሰነ፤ አባ​ትም የል​ጁን ሚስት በኀ​ጢ​አት አረ​ከሰ፤ በአ​ን​ቺም ዘንድ ወን​ድም የአ​ባ​ቱን ልጅ እኅ​ቱን አስ​ነ​ወረ።


የወ​ንድ ልጅ​ህን ሴት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ ወይም የሴት ልጅ​ህን ሴት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ የአ​ንተ ኀፍ​ረተ ሥጋ ነውና።


ከአ​ባ​ትህ የተ​ወ​ለ​ደ​ች​ውን የአ​ባ​ት​ህን ሚስት ልጅ ኀፍ​ረተ ሥጋ አት​ግ​ለጥ፤ ከአ​ባ​ትህ የተ​ወ​ለ​ደች እኅ​ትህ ናት፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን አት​ግ​ለጥ።


“ማና​ቸ​ውም ሰው የአ​ባ​ቱን ልጅ ወይም የእ​ና​ቱን ልጅ እኅ​ቱን ቢያ​ገባ፥ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ቢያይ፥ እር​ስ​ዋም ኀፍ​ረተ ሥጋ​ውን ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕ​ዝ​ባ​ቸ​ውም ልጆች ፊት ይገ​ደሉ፤ የእ​ኅ​ቱን ኀፍ​ረተ ሥጋ ገል​ጦ​አ​ልና ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።


“ከአ​ባቱ ወይም ከእ​ናቱ ልጅ ከእ​ኅቱ ጋር የሚ​ተኛ ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።