የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ያም ሰኰ​ናው ተሰ​ን​ጥ​ቆ​አል፤ ነገር ግን ስለ​ማ​ያ​መ​ሰኳ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዐሣማ ሰኰናው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርያም ሰኮናው ለሁለት ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዐሳማዎችንም አትብሉ፤ እነርሱ ሰኰናቸው የተሰነጠቀ ቢሆንም ስለማያመሰኩ በእናንተ ዘንድ እንደ ርኩስ የሚቈጠሩ ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርያም ሰኮናው ተሰንጥቍል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 11:7
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ቃ​ብ​ርም መካ​ከል የሚ​ተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚ​ያ​ልሙ፥ የእ​ሪያ ሥጋም የሚ​በሉ ናቸው። የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ደምና ዕቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያረ​ክ​ሳሉ።


“በአ​ት​ክ​ልት ቦታ ውስጥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ጠ​ሩና የሚ​ያ​ነጹ፥ በም​ግብ ቦታም የእ​ሪ​ያን ሥጋ፥ አስ​ጸ​ያፊ ነገ​ር​ንም አይ​ጥ​ንም የሚ​በሉ በአ​ን​ድ​ነት ይጠ​ፋሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በሬን የሚ​ሠ​ዋ​ልኝ ኃጥእ ውሻን እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ድ​ልኝ ነው፤ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን የሚ​ያ​ቀ​ር​ብም የእ​ሪ​ያን ደም እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ ነው፤ ዕጣ​ን​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ያ​ጥን አም​ላ​ክን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እነ​ዚህ የገዛ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረጡ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ይላ​ታል።


የተ​ሰ​ነ​ጠቀ ሰኰና ያለ​ው​ንና የሚ​ያ​መ​ሰ​ኳ​ውን እን​ስሳ ሁሉ ብሉ።


ሽኮኮ ያመ​ሰ​ኳል፤ ነገር ግን ሰኰ​ናው ስላ​ል​ተ​ሰ​ነ​ጠቀ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።


የእ​ነ​ዚ​ህን ሥጋ አት​በ​ሉም፤ በድ​ና​ቸ​ው​ንም አት​ነ​ኩም፤ ለእ​ና​ንተ ርኩ​ሳን ናቸው።


በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።


ሄዶም ከዚያ ሀገር ሰዎች ለአ​ንዱ ተቀ​ጠረ፤ እሪ​ያ​ዎ​ች​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ ወደ እር​ሻው ቦታ ሰደ​ደው።


እነ​ዚያ አጋ​ን​ን​ትም ከዚያ ሰው ላይ ወጥ​ተው ወደ እሪ​ያ​ዎች ገቡ፤ የእ​ሪ​ያ​ዎ​ችም መንጋ አብ​ደው ከገ​ደሉ ወደ ባሕር ጠል​ቀው ሞቱ።


እር​ያም፥ ሰኰ​ናው ስለ​ተ​ሰ​ነ​ጠቀ፥ ጥፍ​ሩም ከሁ​ለት ስለ​ተ​ከ​ፈለ፥ ነገር ግን ሰለ​ማ​ያ​መ​ሰኳ፥ እርሱ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋ​ዉን አት​ብሉ፤ በድ​ኑ​ንም አት​ንኩ።