የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቅ​ብ​ዐት ዘይት በላ​ያ​ችሁ ነውና እን​ዳ​ት​ሞቱ ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አት​ውጡ” አላ​ቸው። ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር የመቅቢያ ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን አትውጡ።” እነርሱም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲሁም የጌታ የቅባት ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትውጡ።” እንደ ሙሴ ቃልም አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ባዘዘው የቅባት ዘይት የተቀደሳችሁ ስለ ሆነ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ውጪ አትውጡ፤ አለበለዚያ ትሞታላችሁ፤” አላቸው፤ እነርሱም ሙሴ እንዳዘዛቸው አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔር የቅብዓት ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትወጡም አላቸው። እንደ ሙሴ ቃልም አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 10:7
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ​ንም ሁሉ ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታነ​ጻ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለህ።


የቅ​ብ​ዐ​ት​ንም ዘይት ወስ​ደህ በራሱ ላይ ታፈ​ስ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ባ​ው​ማ​ለህ።


በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን ቅባ​ቸው፤ ቀድ​ሳ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


የአ​ም​ላ​ኩም ቅባት ዘይት ቅዱ​ስ​ነት በላዩ ነውና ከመ​ቅ​ደስ አይ​ውጣ፤ የአ​ም​ላ​ኩ​ንም ቅዱስ ስም አያ​ር​ክስ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ከቅ​ብ​ዐ​ቱም ዘይት በአ​ሮን ራስ ላይ አፈ​ሰሰ፤ ቀባው፤ ቀደ​ሰ​ውም።


ሙሴም ከቅ​ብ​ዐቱ ዘይ​ትና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ከአ​ለው ከደሙ ወስዶ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ ፥ በል​ጆ​ቹና በል​ጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮ​ን​ንና ልብ​ሱ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብስ ቀደሰ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ዘንድ ሙታ​ንን ተዉ​አ​ቸው፤ አንተ ግን ሂድና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ስበክ” አለው።


ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ በኀ​ይ​ልም እንደ ቀባው፥ እየ​ዞ​ረም መል​ካም እንደ አደ​ረገ፥ ሰይ​ጣን ያሸ​ነ​ፋ​ቸ​ው​ንም እንደ ፈወሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ርና።


ከእ​ና​ንተ ጋር በክ​ር​ስ​ቶስ ስም የሚ​ያ​ጸ​ና​ንና የቀ​ባን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።