የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሰቈቃወ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጤት። በሰ​ይፍ የሞ​ቱት በራብ ከሞ​ቱት ይሻ​ላሉ፤ እነ​ዚህ የም​ድ​ርን ፍሬ አጥ​ተው ተወ​ግ​ተ​ውም ዐል​ፈ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በራብ ከሚሞቱት ይልቅ፣ በሰይፍ የተገደሉት ይሻላሉ፤ ምግብ በሜዳ ላይ ካለማግኘታቸው የተነሣ፣ በራብ ደርቀው ያልቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጤት። በሰይፍ የሞቱ በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፥ እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የምድር ምርትን በማጣት ቀስ በቀስ በራብ ከመሞት ይልቅ በጦርነት የሚሞቱት የተሻሉ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጤት። በሰይፍ የሞቱ በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፥ እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል።

ምዕራፉን ተመልከት



ሰቈቃወ 4:9
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ራብ ጸንቶ ነበ​ርና ለሀ​ገሩ ሰዎች እህል ታጣ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አሉ​አ​ቸው፥ “በሥ​ጋው ምን​ቸት አጠ​ገብ ተቀ​ም​ጠን እስ​ክ​ን​ጠ​ግብ ድረስ እን​ጀ​ራና ሥጋ በም​ን​በ​ላ​በት ጊዜ በግ​ብፅ ምድር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ምነው በሞ​ትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልት​ገ​ድሉ እኛን ወደ​ዚች ምድረ በዳ አም​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና።”


ጩኸ​ትና ፍጅ​ትም የተ​ሞ​ላ​ብሽ ከተማ ሆይ፥ ቍስ​ለ​ኞ​ችሽ በሰ​ይፍ የቈ​ሰሉ አይ​ደ​ሉም፤ በአ​ንቺ ውስጥ የተ​ገ​ደ​ሉ​ትም በሰ​ልፍ የተ​ገ​ደሉ አይ​ደ​ሉም።


“በክፉ ሞት ይሞ​ታሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም፤ ነገር ግን በመ​ሬት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ በራ​ብም ይጠ​ፋሉ፤ ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለዱር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናሉ።”


መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ች​ሁም በራ​ሳ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁም በእ​ግ​ራ​ችሁ ይሆ​ናል፤ ዋይ አት​ሉም፤ አታ​ለ​ቅ​ሱ​ምም፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁም ትሰ​ለ​ስ​ላ​ላ​ችሁ፤ ሁላ​ች​ሁም ጓደ​ኞ​ቻ​ች​ሁን ታጽ​ና​ና​ላ​ችሁ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት፦ እና​ንተ፦ በደ​ላ​ች​ንና ኀጢ​አ​ታ​ችን በላ​ያ​ችን አሉ፤ እኛም ሰል​ስ​ለ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ እን​ዴ​ትስ በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን? ብላ​ችሁ ተና​ግ​ራ​ች​ኋል በላ​ቸው።


ደግ​ሞም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እን​ጀራ በትር እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ በች​ግር እያሉ እን​ጀ​ራን በሚ​ዛን ይበ​ላሉ፥ እየ​ደ​ነ​ገ​ጡም ውኃን በልክ ይጠ​ጣሉ፤


ሰይፍ በውጭ፥ ቸነ​ፈ​ርና ራብ በው​ስጥ አለ፤ በሜዳ ያለው በሰ​ይፍ ይሞ​ታል፤ በከ​ተ​ማም ያለ​ውን ቸነ​ፈ​ርና ራብ ይፈ​ጁ​ታል።


ከእ​ና​ን​ተም ተለ​ይ​ተው የቀ​ሩት ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይጠ​ፋሉ፤ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀጢ​አት ደግሞ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ይቀ​ል​ጣሉ።


እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ የከ​ብ​ት​ህን ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ይበ​ላል፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም መንጋ አይ​ተ​ው​ል​ህም።