የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሰቈቃወ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚ​መ​ስሉ የከ​በሩ የጽ​ዮን ልጆች፥ የሸ​ክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እን​ዴት ተቈ​ጠሩ!

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንደ ወርቅ ይቈጠሩ የነበሩ፣ የከበሩ የጽዮን ወንዶች ልጆች፣ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው፣ እንዴት አሁን እንደ ሸክላ ዕቃ ሆኑ!

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚመስሉ የከበሩ የጽዮን ልጆች፥ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እንዴት ተቈጠሩ!

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የከበሩ የጽዮን ልጆች እንደ ንጹሕ ወርቅ ያኽል ውድ ነበሩ፤ እንዴት አሁን የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ ተቈጠሩ!

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚመስሉ የከበሩ የጽዮን ልጆች፥ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እንዴት ተቈጠሩ!

ምዕራፉን ተመልከት



ሰቈቃወ 4:2
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አወ​ዳ​ደ​ቁም እንደ ሸክላ ሠሪ ገንቦ የደ​ቀቀ ይሆ​ናል፤ ሳይ​ራ​ራም ያደ​ቅ​ቀ​ዋል፤ ከስ​ባ​ሪ​ውም እሳት ከማ​ን​ደጃ የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት፥ ወይም ውኃ ከጕ​ድ​ጓድ የሚ​ቀ​ዱ​በት ገል አይ​ገ​ኝም።”


ከወ​ለ​ድ​ሻ​ቸው ልጆ​ችሽ ሁሉ የሚ​ያ​ረ​ጋ​ጋሽ አጣሽ፤ ከአ​ሳ​ደ​ግ​ሻ​ቸ​ውም ልጆ​ችሽ ሁሉ እጁን ሰጥቶ የሚ​ያ​ነ​ሣሽ የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸ​ክላ ሠሪ የሠ​ራ​ውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ከካ​ህ​ናት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤


እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሸ​ክላ ማድጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ባ​በር ደግ​ሞም ይጠ​ገን ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ ይህን ሕዝ​ብና ይህ​ችን ከተማ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​በ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሌላ የለ​ምና በቶ​ፌት ይቀ​በ​ራሉ።


ኢኮ​ን​ያን ተዋ​ረደ፤ ለም​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም የሸ​ክላ ዕቃ ሆነ፤ እር​ሱ​ንና ዘሩን ወደ​ማ​ያ​ው​ቀው ሀገር ወር​ው​ረው ጥለ​ው​ታ​ልና።


ሣን። ብላ​ቴ​ና​ውና ሽማ​ግ​ሌው በመ​ን​ገ​ዶች ላይ ተጋ​ደሙ፤ ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ወድ​ቀ​ዋል፤ በረ​ኃብ ገደ​ል​ሃ​ቸው፤ በቍ​ጣ​ህም ቀን ሳት​ራራ አረ​ድ​ሃ​ቸው።


አለ​ቆች በእ​ጃ​ቸው ተሰ​ቀሉ፤ የሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንም ፊት አላ​ከ​በ​ሩም።


እስ​ራ​ኤል ተው​ጦ​አል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ዛሬ እንደ ግትቻ ዕቃ ሆኖ​አል።


ይሁዳን ለእኔ ገትሬአለሁ፣ ቀስቱን በኤፍሬም ሞልቼአለሁ፣ ጽዮን ሆይ፥ ልጆችሽን በግሪክ ልጆች ላይ አስነሣለሁ፥ አንቺንም እንደ ኃያል ሰው ሰይፍ አደርግሻለሁ።


ነገር ግን ከእኛ ያይ​ደለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገኘ ታላቅ ኀይል ይሆን ዘንድ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ይህ መዝ​ገብ አለን።


በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፤ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤