ሰቈቃወ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዴን በዓለት ላይ ሠራ፤ ጎዳናዬንም አጠረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገዴን በተጠረቡ ድንጋዮች ዘጋ፤ ጐዳናዬንም አጣመመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፤ መተላለፊያዬንም አጣመመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ። |
እስትንፋሱም አሕዛብን ስለ ከንቱ ስሕተታቸው ሊከፋፍላቸው በሸለቆ እንደሚያጥለቀልቅ፥ እስከ አንገትም እንደሚደርስና እንደሚከፋፍል ውኃ ይጐርፋል፤ ስሕተታቸውም ይከተላቸዋል፤ ይወስዳቸዋልም።
አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ፤