የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሰቈቃወ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሄ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠላት ሆነ​ብኝ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን አሰ​ጠመ። አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋን ሁሉ ዋጠ፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋ​ንም አጠፋ። በይ​ሁ​ዳም ሴት ልጅ ውር​ደ​ት​ንና ጕስ​ቍ​ል​ናን አበዛ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፤ እስራኤልንም ዋጠ፤ ቤተ መንግሥቶቿን ሁሉ ዋጠ፤ ምሽጎቿን አፈራረሰ፤ በይሁዳ ሴት ልጅ፣ ልቅሶንና ሰቈቃን አበዛ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሄ። ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፥ እስራኤልን ዋጠ፥ አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፥ አምቦችዋን አጠፋ፥ በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር እንደ ጠላት እስራኤልን አጠፋ፤ ቤተ መንግሥቶችዋን አወደመ፤ ምሽጎችዋን አፈራረሰ፤ በይሁዳ ሕዝብም ለቅሶና ዋይታን አበዛ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሄ። ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፥ እስራኤልን ዋጠ፥ አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፥ አምቦችዋን አጠፋ፥ በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሰቈቃወ 2:5
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የን​ጉ​ሡም የአ​በ​ዛ​ዎች አለቃ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት አቃ​ጠለ። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ሁሉ በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


“ፊት​ህን ከእኔ የሰ​ወ​ርህ፥ እንደ ጠላ​ት​ህም የቈ​ጠ​ር​ኸኝ ስለ​ምን ነው?


በታ​ላቅ ቍጣም ያዘኝ እንደ ጠላ​ትም ቈጠ​ረኝ።


አር​ኤ​ል​ንም አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ፤ ይህ​ችም ኀይል፥ ይህ​ችም ብዕል የእኔ ትሆ​ና​ለች፥


እነ​ርሱ ግን ዐመ​ፁ​በት፤ ቅዱስ መን​ፈ​ሱ​ንም አስ​መ​ረሩ፤ ስለ​ዚህ ተመ​ልሶ ጠላት ሆና​ቸው፤ እር​ሱም ተዋ​ጋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙ​ኤል በፊቴ ቢቆ​ሙም፥ ልቤ ወደ​ዚህ ሕዝብ አያ​ዘ​ነ​ብ​ልም፤ እነ​ዚ​ህን ሕዝ​ቦች ከፊቴ አባ​ር​ራ​ቸው፤ ይውጡ።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ በቅ​ጥ​ርም ውጭ የከ​በ​ቡ​አ​ች​ሁን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን የም​ት​ወ​ጉ​በ​ትን በእ​ጃ​ችሁ ያለ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም በዚ​ህች ከተማ መካ​ከል እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ወዳ​ጆ​ችህ ሁሉ ረስ​ተ​ው​ሃል፤ አይ​ፈ​ል​ጉ​ህ​ምም፤ በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ በጠ​ላት ማቍ​ሰ​ልና በጨ​ካኝ ቅጣት አቍ​ስ​ዬ​ሃ​ለ​ሁና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት አቃ​ጠለ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ሁሉ ፥ ታላ​ላ​ቆ​ችን ቤቶች ሁሉ፥ በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


ቤት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የያ​ዕ​ቆ​ብን መል​ካም ነገር ሁሉ አሰ​ጠመ፤ አል​ራ​ራ​ምም፤ በመ​ዓቱ የይ​ሁ​ዳን ሴት ልጅ አን​ባ​ዎች አፈ​ረሰ፤ ወደ ምድ​ርም አወ​ረ​ዳ​ቸው፤ መን​ግ​ሥ​ቷ​ንና ግዛ​ቷ​ንም አረ​ከሰ።


ዳሌጥ። ቀስ​ቱን እንደ ተቃ​ዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላ​ጋ​ራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽ​ዮን ሴት ልጅ ድን​ኳን ለዐ​ይኑ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ሁሉ ገደለ፤ መዓ​ቱ​ንም እንደ እሳት አፈ​ሰሰ።


በፊ​ቴም ዘረ​ጋው፤ በው​ስ​ጥና በው​ጭም ተጽ​ፎ​በት ነበረ፤ ጽሑ​ፉም “ልቅ​ሶና ኀዘን፥ ዋይ​ታም” ይል ነበር።


ሳሙ​ኤ​ልም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከራ​ቀህ፥ ወደ ባል​ን​ጀ​ራ​ህም ከተ​መ​ለሰ ለምን ትጠ​ይ​ቀ​ኛ​ለህ?