እንዲህም አለኝ፥ “ይህ ሕዝብ፦ ከባድ ነው የሚለውን ሁሉ፦ ከባድ ነው አትበሉ፤ መፈራታቸውንም አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
ኢያሱ 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከእርሱም ጋር የነበሩ ተዋጊዎች ሁሉ፥ ጽኑዓን ኀያላኑም ሁሉ ከጌልጌላ ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱ ምርጥ የሆኑትን ተዋጊዎች ሁሉ ጨምሮ ሰራዊቱን በሙሉ ይዞ ከጌልገላ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ከእርሱም ጋር የነበሩ ተዋጊዎች ሁሉ ጽኑዓን ኃያላኑም ሁሉ ከጌልገላ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ኢያሱና መላው ሠራዊት፥ ምርጥ የሆኑት ወታደሮች ጭምር ከጌልጌላ ወጥተው ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰልፈኞች ሁሉ ጽኑዓን ኃያላኑም ሁሉ ከጌልገላ ወጡ። |
እንዲህም አለኝ፥ “ይህ ሕዝብ፦ ከባድ ነው የሚለውን ሁሉ፦ ከባድ ነው አትበሉ፤ መፈራታቸውንም አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
ብታምንበት ይቀድስሃል፤ እንደ ድንጋይ ዕንቅፋትም አያደናቅፍህም፤ እንደሚያድጥ ዓለትም አይሆንብህም፤ ሁለቱ የያዕቆብ ቤቶች ግን በኢየሩሳሌም በወጥመድና በአሽክላ ተይዘው ይኖራሉ።
የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው፥ “ባሪያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፤ በተራራማው ሀገር የሚኖሩ የአሞሬዎናውያን ነገሥት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ፤ አድነንም፤ ርዳንም፤” አሉት።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “አትፍራ፤ አትደንግጥ፤ ተዋጊዎችን ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ፤ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እነሆ፥ የጋይንም ንጉሥ፥ ሕዝቡንም ከተማውንም ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ።
ኢያሱም፥ ተዋጊዎቹም ሕዝብ ሁሉ ተነሥተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያሱም ጽኑዓን፥ ተዋጊዎችና ኀያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌሊትም ላካቸው።