የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊ​ና​ቸው ወቅ​ሶ​አ​ቸው ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጀምሮ እስከ ኋለ​ኞቹ ድረስ፥ አን​ዳ​ንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ብቻ​ውን ቀረ፤ ሴት​ዮ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከል ቆማ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህን እንደ ሰሙ፣ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ በአንድ ወጡ፤ ሴትዮዋም እዚያው ፊቱ እንደ ቆመች ኢየሱስ ብቻውን ቀረ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ከሽማግሌዎች ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ከዚያ ሄዱ፤ ስለዚህ ኢየሱስ በመካከል ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ብቻውን ቀረ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸዋና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 8:9
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ስ​ዋም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? አን​ተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ታሳ​ስብ ዘንድ፥ ልጄ​ንስ ትገ​ድል ዘንድ ወደ እኔ መጥ​ተ​ሃ​ልን?” አለ​ችው።


ንጉ​ሡም ደግሞ ሳሚን፥ “አንተ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ላይ የሠ​ራ​ኸ​ውን፥ ልብ​ህም ያሰ​በ​ውን ክፋት ሁሉ ታው​ቃ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋ​ት​ህን በራ​ስህ ላይ ይመ​ል​ሳል።


ሰማይ ኀጢ​ኣ​ቱን ይገ​ል​ጥ​በ​ታል፤ ምድ​ርም በእ​ርሱ ላይ ትነ​ሣ​ለች።


የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።


ለድ​ሃና ለም​ስ​ኪን ይራ​ራል፥ የድ​ሆ​ች​ንም ነፍስ ያድ​ናል።


ብዙ ጊዜ ያበ​ሳ​ጭ​ሃ​ልና፤ በብዙ መን​ገ​ድም ልብ​ህን ያስ​ከ​ፋ​ታ​ልና፥ አንተ ደግሞ ሌሎ​ችን እንደ ረገ​ምህ ታው​ቃ​ለ​ህና።


ይህ​ንም ባለ ጊዜ በእ​ርሱ ላይ በጠ​ላ​ት​ነት የተ​ነ​ሡ​በት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእ​ርሱ ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ቀና ብሎ ወደ እር​ስዋ ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት፥ የሚ​ከ​ሱሽ ወዴት አሉ?”


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ፤ የሚ​ከ​ተ​ለኝ የሕ​ይ​ወት ብር​ሃ​ንን ያገ​ኛል እንጂ በጨ​ለማ ውስጥ አይ​መ​ላ​ለ​ስም” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም በዝ​ሙት የተ​ያ​ዘች ሴት ወደ እርሱ አም​ጥ​ተው በመ​ካ​ከል አቆ​ሙ​አት።


ዳግ​መ​ኛም ጐን​በስ ብሎ በጣቱ በም​ድር ላይ ጻፈ።


በል​ባ​ቸው የተ​ጻ​ፈ​ውን የሕግ ሥራ ያሳ​ያሉ፤ ከሥ​ራ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ይታ​ወ​ቃል፤ ሕሊ​ና​ቸ​ውም ይመ​ሰ​ክ​ር​ባ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ልም።


አታ​መ​ን​ዝሩ ትላ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለህ፤ ወደ ጐል​ማሳ ሚስ​ትም ትሄ​ዳ​ለህ፤ ጣዖ​ትን ትጸ​የ​ፋ​ለህ፤ አንተ ግን ቤተ መቅ​ደ​ስን ትዘ​ር​ፋ​ለህ።