የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሲፈ​ት​ነው ይህን አለ እንጂ፥ እር​ሱስ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ያውቅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህን የጠየቀው ሊፈትነው እንጂ ራሱ ሊያደርግ ያሰበውን ያውቅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሊፈትነው ይህን ተናገረ፤ እራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስ ይህን የተናገረው ፊልጶስን ለመፈተን ነበር እንጂ፥ የሚያደርገውንስ እርሱ ራሱ ያውቅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና ሊፈትነው ይህን ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 6:6
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች በኋላ እን​ዲህ ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን ፈተ​ነው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አብ​ር​ሃም! አብ​ር​ሃም ሆይ፥” እር​ሱም፥ “እነሆ፥ አለሁ” አለ።


ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን መሳ​ፍ​ንት መል​እ​ክ​ተ​ኞች በሀ​ገሩ ላይ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተ​ላኩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ነ​ውና በልቡ ያለ​ውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።


በሃ​ይ​ማ​ኖት ጸን​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ራሳ​ች​ሁን መር​ምሩ፤ እና​ንተ ራሳ​ች​ሁን ፈትኑ፤ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳለ አታ​ው​ቁ​ምን? እን​ዲህ ካል​ሆነ ግን እና​ንተ የተ​ና​ቃ​ችሁ ናችሁ።


አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ትወ​ድ​ዱት እን​ደ​ሆን ያውቅ ዘንድ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊፈ​ት​ና​ችሁ ነውና የዚ​ያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አት​ስሙ።


ስለ ሌዊም እን​ዲህ አለ፥ ለሌዊ ቃሉን፥ በመ​ከ​ራም ለፈ​ተ​ኑት፥ በክ​ር​ክር ውኃም ለሰ​ደ​ቡት፥ ለእ​ው​ነ​ተ​ኛው ሰው ጽድ​ቁን መልስ።


በመ​ጨ​ረ​ሻም ዘመን መል​ካም ያደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ ሊፈ​ት​ንህ፥ ሊያ​ዋ​ር​ድ​ህም አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቁ​ትን መና በም​ድረ በዳ የመ​ገ​በ​ህን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ፥


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ንህ ዘንድ፥ በል​ብ​ህም ያለ​ውን ትእ​ዛ​ዙን ትጠ​ብቅ ወይም አት​ጠ​ብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ በም​ድረ በዳ የመ​ራ​ህን መን​ገድ ሁሉ አስብ።


“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ ‘ሐዋርያት ነን’ የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤