የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 20:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በፍ​ታ​ዉ​ንም በአ​ንድ ወገን ተቀ​ምጦ አየ፤ በራሱ ላይ የነ​በ​ረው መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያም ሳይ​ቃ​ወስ ለብ​ቻው ተጠ​ቅ​ልሎ አየ፤ ከበ​ፍ​ታዉ ጋርም አል​ነ​በ​ረም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲሁም በኢየሱስ ራስ ላይ ተጠምጥሞ የነበረውን ጨርቅ አየ፤ ይህም ጨርቅ ከከፈኑ ተለይቶ እንደ ተጠቀለለ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲሁም በራሱ ላይ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳልነበረ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኢየሱስ ራስ ተጠምጥሞ የነበረበት ጨርቅ ከከፈኑ ጨርቅ ጋር ሳይሆን ለብቻው በሌላ ስፍራ ተጠቅሎ እንደ ተቀመጠ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ደግሞም በራሱ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳልነበረ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 20:7
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሦስ​ተ​ኛ​ውም መጥቶ እን​ዲህ አለው፦ አቤቱ፥ በእኔ ዘንድ የነ​በ​ረ​ቺው ምና​ንህ እነ​ኋት፤ በጨ​ርቅ ጠቅ​ልዬ አኑ​ሬ​አት ነበር።


ሞቶ የነ​በ​ረ​ውም እንደ ተገ​ነዘ፥ እጁ​ንና እግ​ሩ​ንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰ​በን እንደ ተጠ​ቀ​ለለ ወጣ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ፍቱ​ትና ተዉት ይሂድ” አላ​ቸው።


እንደ አይ​ሁድ አገ​ና​ነዝ ሥር​ዐ​ትም የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወስ​ደው ከሽቱ ጋር በበ​ፍታ ገነ​ዙት።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ተከ​ት​ሎት ደረ​ሰና ወደ መቃ​ብሩ ገባ፤